Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወ/ሮ አዳነች ከካቢኔ አባላት ጋር የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከካቢኔ አባላት ጋር የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ጎብኝተዋል።
 
ጉብኝቱ አየር ሃይሉ እያካሄደ ያለውን ሪፎርም እና ለውጥ ለማየት እና የከተማ አስተዳደሩ የሚችለውን ድጋፍ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
 
የኢትዮጵያ ኩራት የሆነውን የአየር ሃይል ከዚህ ቀደም ትኩረት ያልተሰጠው እና ከአቅሙ በታች ይሰራ የነበረ ተቋም መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ አዳነች÷ አሁን ላይ መሰረታዊ ሪፎርም ተደርጎለት በዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ሃይል ማፍራት በሚችል ደረጃ ላይ መሆኑን መመልከት ችለናል ብለዋል።
 
አየር ሃይሉ የኢትዮጵያን ዓላዊነት በማስጠበቅ አኩሪ ገድል እየፈጸመ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
 
የከተማ አስተዳደሩም ለአየር ሃይል አባላት ደጀንነቱን ለመግለጽ የሰንጋ በሬዎችን ድጋፍ ማድረጉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በኢትዮጵያ አየር ሃይል በተካሄደው የጉብኝት መርሃግብር የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የካቢኔ አባላት ተሳትፈዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version