Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ህውሓት ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች ሁሉ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት መጋዘኖችን ዘርፏል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት መጋዘኖችን እንደዘረፈ በኢትዮጵያ የድርጅቱ ሚሽን ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ህወሓት ሁኔታውን ያለአግባብ እየተጠቀመበት እንደሆነ እናምናለን ብለዋል፡፡
ከተረጂዎች ላይ እርዳታን በሃይል እየነጠቀ እንደሆነ ይሰማናል ያሉት ዳይሬከተሩ÷ እርግጠኛ ሆነን መናገር የምንችለው ግን የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አባላት ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ ያሉትን የእርዳታ መጋዘኖቻችንን ዘርፈዋል፡፡
የህወሓት ወታደሮች በገቡባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሁሉ የእርዳታ መጋዘኖችን ዘርፈዋል፣ መኪኖችን ሰርቀዋል በየመንደሮቹ ብዙ ውድመትን አድርሰዋልብለዋል፡፡
ይህ ደግሞ ለተጎጂዎቹም ሆነ ለእኛ ለረጂዎቹ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ም ነው ያስረዱት፡፡
ኢትዮጵያ ዓለም ላይ ካሉ ምርጥ አጋሮቻችን መካከል አንዷ ነች ያሉት ዳይሬክተሩ÷ ከኢትዮጵያ ጋር ስላለን አጋርነት በእጅጉ እንጨነቃለንም ብለዋል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ህብረተሰቡ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሚሰራጩትን ያልተረጋገጡ ወሬዎች በመያዝ የኢትዮ አሜሪካ ግንኙነት እንደሻከረ ያስባሉ ያሉት ጆንስ÷ ነገር ግን እንደአሁኑ ከኢትዮጵያ ጋር ተባብረን የሰራንበት ጊዜ የለምም ነው ያሉት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version