Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ደረጃውን የጠበቀ የበግ ቆዳ በማምረት ውጤት ላስመዘገቡ ፋብሪካዎች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ ጥራት ያለው የኢትዮጵያ የበግ ቆዳ በማምረት ውጤት ላስመዘገቡ አራት ፋብሪካዎች ዕውቅና ተሰጣቸው፡፡
 
በዘርፉ ዕውቅና ያገኙ ፋብሪካዎችም ባህርዳር፣ ኒው ዊንግ ፣ ፒታርድ እና ኤሊኮ የተሰኙ የቆዳ ፋብሪካዎች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር አስታውቋል፡፡
 
የቆዳ ፋብሪካዎቹ ደረጃውን የጠበቀ እና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳጅነት ያተረፈ የኢትዮጵያ የበግ ቆዳ በማምረት ነው ዕውቅና እና ሰርተፍኬት የተሰጣቸው ፡፡
 
በጃይካ የቴክኒክ እና ገንዘብ ድጋፍ የቆዳ ፋብሪካዎቹ ከፍተኛ ጥራት ያለውን እና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳጅነት ያተረፈውን የኢትዮጵያ ደጋ የበግ ቆዳ እንዲያመርቱ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡
 
ለዚህም የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር፣ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢኒስቲቲዩት ከጃፓን የቴክኒክ ተራድኦ ድርጅት “ጃይካ” ጋር በቅንጅት መስራታቸውን ከማህበሩ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በቀጣይም በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥራቱ እና በተመራጭነቱ ቀዳሚ የሆነውን የኢትዮጵያ የበግ ቆዳ ምርት በስፋት ለማስተዋወቅ የተለያዩ እቅዶችን በመቅረጽ እየተሰራ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version