Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአፋር እና አማራ ክልሎች የሰብዓዊ ድጋፍ ክንውን ያለበት ደረጃ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል የሚኒስትሮች ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡

በውይይቱ በአፋር እና አማራ ክልልሎች የሰብዓዊ ድጋፍ ክንውን ያለበት ደረጃ፣ የሴክተር መስሪያ ቤቶች ክንውን፣ ልዩ ትኩረት የሚሹ አካባቢዎች ላይ የተለየ ትኩረት በመስጠት ድጋፍ የሚከናወንበት አግባብ፣ በሂደቱ ያሉ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ያሉበት ደረጃ፣ እንዲሁም በአጠቃላይ የመልሶ ማቋቋም እቅድ ዝግጅት መጀመር እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራትን ለማሳለጥ ከፌደራል እና ክልል የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች መንቀሳቀሱ ተመልክቷል።

በመጨረሻም የኮሚቴው ሰብሳቢ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ቀጣይ ክንውኖች ላይ አቅጣጫ መስጠታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version