አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሀገርን ለማዳን ከሚደረገው የህልውና ዘመቻ ባሻገር የልማት ስራዎች በትጋት በመስራት ትግል ማድረግ እንደሚገባ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተደድር አቶ እርስቱ ይርዳው ተናገሩ፡፡
ሀገርን ለማስከበር በሚደረግ ሒደት መላው ህዝብ ድል እያስመዘገበ እንደሚገኝና ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ህዝቡም በተለያየ መንገድ እያደረገ ያለውን ድጋፍም የበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በተለይ በግብርናው ዘርፍ ላይ የተሰራው ስራ ከራስ አልፎ ለሀገር የሚተርፍ ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ኩታ ገጠም የአመራረት ዘዴ በክልሉ በአብዛኛው አካባቢዎች ተግባራዊ የተደረገና ምርታማነትን የሚያሳድግ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
በደቡብ ክልል በበልግና በመኸር እርሻ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ዛሬ የመስክ ጉብኝት በተደረገበት ወቅት አቶ እርስቱ ይርዳው የመስክ ምልከታው ሀገሪቱ መበልፀግ እንደምትች በተግባር ያየንበት ነው ብለዋል፡፡
በመስክ ምልከታው የበልግ የምርት ዘመን የምርት ቅናሽ ሊኖር እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ በ2013/14 ቀጣይ የእርሻ ወቅቶች ላይ ማካካሻ ሊያመጣ በሚቻልባቸው ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
በምርት ሒደቱም በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ በመከናወን ላይ መሆኑንና ከ75 በመቶ በላይ የሚሆነው መሬት በኩታ ገጠም እየለማ ይገኛል ተብሏል፡፡
በብርሃኑ በጋሻዉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

