አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ህወሓት “ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች ላይ እያደረሰ ያለው ውድመት እጅግ አስነዋሪና በጦር ወንጀለኝነት መታየት ያለበት ድርጊት ነው” ሲል አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ተናገረ፡፡
“ማን ከማን ጋር እንኳ እንደተጋጩ የማያውቁ ህጻናትን ትምህርት ቤት ማውደም በምን ይገላጻል?” በማለት ነው በምሬት የጠየቀው፡፡
አትሌቱ በአማራ ክልል በዋግ ኸምራ ዞን ፃግብጂ ወረዳ በዳስ ጥላ ለሚማሩ ህጻናት ያስገነባው ትምህርት ቤት በመውደሙ እጅግ እንዳዘነም ነው የገለጸው፡፡
ትምህርት ቤቱን ለመገንባት ከገንዘብ ወጪ በላይ በርካታ ውጣ ውረዶችን እንዳሳለፈ የገለጸው አትሌቱ÷ የትምህርት ቤቱ መውደም በአካባቢው ማህበረሰብ ቁስል ላይ እንጨት እንደመስደድ ይቆጠራል ነው ያለው፡፡
አትሌቱ ያስገነባውን ጨምሮ በአካባቢው በርካታ ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎች መውደማቸውን ጠቅሶ፤ ይህም የአሸባሪው ህወሃትን “የክፋት ጥግ ያሳያል” በማለት አስረድቷል፡፡
በየትኛውም ዓለም በሚካሄዱ ጦርነቶች ትምህርት ቤቶችና ሆስፒታሎችን ዒላማ ማድረግ የጦር ወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑንም አትሌት ሻለቃ ሃይለ ገብረስላሴ መናገሩን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ትምህርት ቤቱም ከአምስት መቶ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ህጻናት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

