አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ሱማሌ ተራ አካባቢ የሚገኘው የአሙዲ ተስፋ ብርሃን የምግባ ማዕከል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ከ2 ሺህ በላይ ወገኖች የማዕድ ማጋራት ተካሄደ፡፡
በማዕከሉ የማዕድ ማጋራት ሥነ-ሥርዓት ላይ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ መገኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በሥነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት በዓለን ከእናንተ ጋር ማክበር በመቻሌ ደስተኛ ነኝ ብለዋል፡፡
በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ማግኘት የማይችሉ ወገኖችን ለመመገብ የተቋቋመው አሙዲ የተስፋ ብርሐን የምግባ ማዕከል የአንድ አመት ወጭ የሚሸፍነው የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩም መሆኑ ይታወቃል፡፡
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በስድሰቱም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የምገባ ማዕከላት ለወገኖች የማዕድ ማጋራት እያደረገ መሆኑን አቶ ጀማል አህመድ ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

