አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የተመራ የልዑካን ቡድን ባሕር ዳር ገብቷል፡፡
ልዑካኑ ባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራው ልዑክ ባሕር ዳር የገባው በሕልውና ዘመቻው ለተፈናቀሉ የአማራ ክልል ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡
ወይዘሮ አዳነች በቆይታቸው ከአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር እና ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ክልሉ በአሸባሪው ቡድን ወረራ በደረሰበት ጉዳት እና በዘላቂነት በሚደረጉ ድጋፎች ዙሪያ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የሲቭክ ማኅበራትና ተቋማት ተወካዮች የልዑኩ አባላት ናቸው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

