አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄን በመቀላቀል ፊርማቸውን አኖሩ።
የኢትዮጵያን እውነታ ለመላው ዓለም ለማሳወቅ ዓላማ ያደረገው “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅንቄ መጀመሩ ይታወቃል።
የንቅናቄው ዓላማ የአገር ጉዳይ በመሆኑ በዘመቻው በመሳተፍ ግደታችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ሲሉ የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናግረዋል።
በተለየም በአንዳንድ ምዕራብያዊን ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ላይ የተዛባና የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ይህንን የተቀናጀ ዘመቻ በጋራ መመከት ይገባል ያሉት የፓርቲዎቹ አመራሮች “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄን መቀላቀላቸውን ይፋ አድርገዋል።
በንቅናቄው የኢትዮጵያን እውነተኛ መረጃ ለዓለም ማህበረሰብ ሁላችንም ማድረስና ማስረዳትም ይጠበቅብናል ነው ያሉት።
የሽብርተኛውን ህወሓት አገር የማፍረስ ሴራ እንዲሁም የጅምላ ግዲያና ዘረፋ ዓለም እንዲያውቀው ማድረግ ይገባል ብለዋል ፓርቲዎቹ።
በዛሬው እለት አቶ ማሙሸት አማረ፣ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ አቶ ሙሳ አደም እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ራሄል ባፌ ተገኝተው “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ዘመቻ ፊርማቸውን ማኖራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
“የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት” መርሃ ግብር እስከ መስከረም15 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

