Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የክልሉ ጤና ቢሮ ለ15አመታት የሚጠቀምበትን የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ እና የ10አመት የምግብና ስርዓተ ምግብ ስትራቴጂ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ የክልል ጤና ቢሮ ለቀጣይ 15አመታት የሚጠቀምበትን የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ እና የ10አመት የምግብና ስርዓተ ምግብ ስትራቴጂ ይፋ አድርጓል፡፡
ቢሮው ፍኖተ ካርታውን በወላይታ ሶዶ ይፋ ሲያደርግ የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ ላለፉት 15አመታት ስራ ላይ የቆየው የጤና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብር ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ገልፀው በዚህም በክልሉ የወባ፣ ቲቢ፣ ኤች አይ ቪ፣ የእናቶችና ህፃናት ሞት መቀነስ ተችሏል ብለዋል፡፡
መርሃ ግብሩ ለውጥ ያመጣ ቢሆንም ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ በአዲስ ፍኖተ ካርታ መቀየር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ለቀጣይ 15 ዓመታ እንዲያገለግል ታስቦ ተዘጋጅቷ ብለዋል፡፡
የጤና ኬላዎችን በመሠረተ ልማት ማጠናከርና በሙያተኛ ማደራጀት ትኩረት እደሚሰጠውም ነው የገለፁት፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ ፍኖተ ካርታው ገቢር እንዲሆን የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ሃብት የማሰባሰብና አጋሮችን የማስተባበር ስራ ይተገበራልም ነው የተባለው፡፡
በኤርሚያስ ቦጋለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version