Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአማራ ክልል ህወሓት ከ20 በላይ ሆስፒታሎች እና 277 የጤና ጣቢዎችን አውድሟል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ሚንስቴር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የተመራ ልዑካን ቡድን ጉዳት የደረሰባቸዉን የጤና ተቋማት ጎብኝቷል፡፡
በጉብኝቱ ከጤና ሚኒስትር ፣ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ የተዉጣጡ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ ወረራ በፈጸመባቸዉ የክልሉ አካባቢዎች 20 ሆስፒታሎች እና 277 የጤና ኬላዎች እንዲሁም 2 የደም ባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት አገልግሎት መስጠት አቁመዋል፡፡
ከነዚህ ዉስጥ 14 ሆስፒታሎች፣ 153 የጤና ጣቢያዎች፣ 642 የጤና ኬላዎችና 29 አምቡላንሶች ሙሉ በሙሉ መዉደማቸዉን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ታሪኩ በላቸዉ ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱ የተገኙት በጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ሕጻናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም በበኩላቸዉ በሽብር ቡድኑ የደረሰዉ ጉዳት ከስብዕና በታች የሆነና በኢትዮጵያም ሆነ በአለም ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ነዉ፡፡
የወደሙ የጤና ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ በፌዴራል እና በክልል ጤና ተቋማት ህረተሰቡን በማሳተፍ የአጭርና የረዥም ጊዜ እቅድ ተይዞ እንዲሁም እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version