አዲስ አበባ፣ መስከረም 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ዩኒቨርሲት በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ9 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ወልዱ አሰፋ እንደገለጹት÷ ዩኒቨርሲቲዎች የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባር ሀላፊነታቸው በመሆኑ በሦስት የሀገራችን አካባቢዎች በመገኘት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ÷ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት 2 ነጥብ 4፣ በወሎ ዩኒቨርሲቲ 2 ነጥብ 45 እና በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ 4 ነጥብ 15 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓልም ነው የተባለው፡፡
አቶ ወልዱ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት÷ በአሸባሪው ህወሓት ከተፈናቀሉት ወገኖች ጎን መሆናችንን ለማሳየት ነው እንጅ ድጋፉ በቂ እንዳልሆነ እናምናለን ብለዋል፡፡
የወሎ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳሬክተር እና የድጋፍ ማሠባሠብ አስተባባሪ ዶክተር ጌታቸው ጉግሳ በበኩላቸው÷ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ያደረገውን ድጋፍ አመስግነው የዩኒቨርሲቲዎች ትስስር በዚሁ ሊቀጥል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
በአለባቸው አባተ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

