Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የስሚንቶ እጥረትን ለመቀነስ እየሰራሁ ነዉ-የንግድና ኢንዱሰትሪ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ)የስሚንቶ ምርት እጥረትን ለመቀነስ እና የተረጋጋ ዋጋ እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢኮኖሚ አሻጥር በስሚንቶ ምርት ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስና የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር የተቋቋመ ግብረ- ሀይል ከሲሚንቶ አከፋፋዮችና ባለድርሻ አካለት ጋር ተወያይቷል፡፡
በሚኒስቴሩ የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ሀብታሙ አራጌ እንደገለጹት÷ የስሚንቶ ምርት አቅርቦትን የሚመራ ኮሚቴ የሲሚንቶ አከፋፋዮችንና ቸርቻሪዎችን የሚጠቅም እንደ ኮሚቴ በተነጋገርነው መሰረት ገበያው ሳይረበሽ የተረጋጋ ዋጋ እንዲኖረው፣ አከፋፋዩም ነጻ ሆኖ የሚሰራበት ሁኔታን ማመቻቸት እንጅ አዲስ መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኮሚቴው የስሚንቶ ምርት አቅርቦት ማሻሻልና የተረጋጋ የሲሚንቶ ግብይት ስርዓትን ለመፍጠር ዓላማ ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የሲሚንቶ እጥረቱ ሊቀረፍ የሚችለውም ፋብሪካዎች ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመቅረፍ የማምረት አቅም በመጨመር ነው ብለዋ፡፡
አሁን ላይም በቀን 195ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ እየተመረተ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የዘርፉን ችግር ለመፍታት በቀን ወደ 240ሺህ ኩንታል የማምረት አቅም እንዲኖር በማድረግ ከዚህም ውስጥ 80ሺህ ኩንታል ወደ ገበያ እንዲገባ በማድረግ ገበያውን ለማረጋገት እየተሰራ ነው ማለታቸዉን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version