አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ6ተኛው ዙር የምክር ቤት አባላት በምክር ቤቱ አሠራር ዙሪያ ሥልጠና እየሠጠ ነው፡፡
ዛሬ የተጀመረው የምክር ቤት አባላት ሥልጠና በዋናነት በምክር ቤቱ አሠራሮች፣ ሥነ-ሥርዓቶች፣ ደንቦችና ጽህፈት ቤቱ በሚሠጠው አገልግሎት ዙሪያ ማስተዋወቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
በስልጠናውም ምርጫ ካልተደረገባቸው አካባቢዎች በስተቀር በሀገሪቱ በሚገኙ የምርጫ ክልሎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአባልነት የተመረጡ ሁሉ ተሣታፊ ሆነዋል፡፡
6ተኛው ዙር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 24/2014 ዓ.ም የመንግስት ምስረታ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡
ስልጠናው ከወዲሁ አባላቱ በምክር ቤቱ አሠራርና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታሣቢ ተደርጐ የተዘጋጀ መሆኑን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

