አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ለተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ድጋፍ አደረገ፡፡
ዩኒቨርስቲው ለህክምናና ለመማርያ የሚሆነውን ድጋፉ ያደረገው ለጌዴኦ ዞን ጤና ተቋማትና ትምህርት መምሪያ፣ ለሲዳማ ክልል ቀባዶ ወረዳ እና በደቡብ ክልል ለአማሮ ልዩ ወረዳ መሆኑ ተመላክቷል።
ድጋፉ በአይነት 217 የህክምና ቁሳቁሶችን ያካተተ መሆኑን የዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፌራል ሆስፒታል ምክትል ኘሬዝዳንት ዶክተር ሰላማዊት አየለ ተናግረዋል።
አቶ ናፍቆት ብርሃኑ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ በበኩላቸው፥ የተደረገውን ድጋፍ በጥንቃቄና በአግባቡ በመያዝ ስራ ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳዊት ሀየሶ ፥በዩኒቨርሲቲው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ የመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ በቀጣይ ስልጠና በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ ስልጠና እየሰጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከጌዲኦ ዞን ህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share

