አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ህዝብ ያለ ምንም ልዩነት በአንድነት ወጥቶ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቶቹን ጠብቆ እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።
በቢሮው የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ቶላ እንደገለጹት÷ በዓሉ የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት በመውጣት ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት የሰላምና የፍቅር በዓል ነው።
ይሄን ህዝባዊ በዓል ተገቢ ካልሆነ እንቅስቃሴ በመከላከል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል።
በኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና በመገናኛ ብዙሃን በተደረገ ጥረት በተለይም ካለፉት አስር አመታት ወዲህ ህዝቡ በእሬቻ ባህላዊ እሴቶች ላይ ያለው መረዳት እያደገ መምጣቱን ባለሙያው ገልጸዋል።
ለዚህ ደግሞ “ቀልቡን ሰብስቦና ውስጡን ከቂም በቀል አፅድቶ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት የተረጋጋና ፀጥ ያለ ቦታ ያስፈልገዋል” ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

