አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ እና የልዑካን ቡድናቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀድሞ የተማሩበትን የበሻሻ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎበኙ፡፡
በጉብኝታቸው ÷ ተማሪዎቹ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሀገር ተረካቢ ለመሆን ጠንክረው እንዲማሩና ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
ለአንድ ሀገር ግንባታ ትምህርት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰውም ወላጆች ልጆቻቸው ወደ ትምህርት ቤት በመላክና የልጆቻቸውን ትምህርት መከታተል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ የአካባቢው አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ትምህርት ቤቱ አሁን ያለበትን ደረጃና ያጋጠሟቸውን ችግሮች ለሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ቤቱን ለማደስና ምቹ የመማር ማስተማር ሂደትን ለመፍጠር የሚያስችል ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀድሞ የተማሩበትን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉበት የበደሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትንም አክለው ጎብኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

