Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሜሪካ ከ453 ሺህ በላይ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰኘውን 453ሺህ 600 የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረጓ ተገለጸ።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ለጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ድጋፉ በዛሬው ዕለት በጃንሜዳ ጤና ጣቢያ አስረክበዋል።
ኢዜአ ከአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ እንደዘገበው ፥ በዛሬው ዕለት ድጋፍ የተደረገው የኮሮና መከላከያ ክትባት 453 ሺህ 600 የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተሰኘው ክትባት ነው።
በተጨማሪም 504ሺ ክትባቶች በቀጣይ ድጋፍ እንደሚደረግ ኤምባሲው አስታውቋል።
አሁን የተደረገውን ድጋፍ ጨምሮ አሜሪካ እስካሁን ለኢትዮጵያ 2.6 ሚሊዮን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶችን ድጋፍ ማድረጓ ታውቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
Exit mobile version