Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የህዳሴ ግድቡ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ አለው- የዩጋንዳ የውሃና አካባቢ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩጋንዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዓለም ፀሐይ መሰረት ከዩጋንዳ የውሃና አካባቢ ሚኒስትር ሳም ቺፕቶሪስ ጋር ተወያዩ፡፡
በታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ በአረንጓዴ አሻራ በጎ ልምድ እና ወደ ጎረቤት ሀገራት ስለሚስፋፋበት ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ በቅርቡ መንግስት እንደሚመሰረት፣ የህወሓት አሸባሪ ቡድን መንግስት ያደረገውን የተናጠል ተኩስ አቁም እርምጃ ባለመቀበል ህፃናትን ወደ ጦርነት እየማገደ መሆኑን፣ በአማራና አፋር ክልሎች የሚገኙ ንፁሃን ዜጎችን በግፍ እያጠቃ እና መሰረተ ልማቶችን እያወደመ ስለመሆኑ አምባሳደሯ አብራርተውላቸዋል፡፡
ሳም ቺፕቶሪስ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በትኩረት እደሚከታተሉ ጠቅሰው ኢትዮጵያ ችግሮችን የመፍታት አቅም እንዳላት መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘም በተፋሰሱ አገራት መካከል ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ውጤት ላይ ለመድረስ በቅንነት መደራደር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የግድቡ መገንባት በተፋሰሱ አገራት የውሃን ፍሰት ከመቆጣጠር ጀምሮ በኤሌክትሪክ ኃይል በማስተሳሰር ረገድ ከሚኖረው ጠቀሜታ አኳያ የህዳሴ ግድቡ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአረንጎዴ አሻራ መርሃ ግብር አካባቢን ለመጠበቅ እያደረገች ያለውን ሰፊ እንቅስቃሴ እንደሚያደንቁና ይኑ በጎ ልምድ ወደ ዩጋንዳ መውሰድ እንደሚፈልጉም ነው የገለጹት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version