አዲስ አበባ፣መሰከረም 13፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ በእንግሊዝ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ የሚያደረግ መመሪያ በደጋሜ ወጣ፡፡
ካሁን በፊት ተማሪዎች የኮሮና ቫይረስ ክትባት ከወሰዱ ያለ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ትምህርታቸዉን መከታተል ይችሉ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ የቫይረሱ ስርጭት ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ተማሪዎች ጭምብል እንዲጠቀሙ መመሪያ ተሠጥቷል፡፡
ጊሲሌ ሊንክ በኦገሰቲን ካተሪበሪ ተምህርት ቤት ርዕሰ መምህር÷ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ትመህርት ቤታቸዉ ከተከፈተ በኋላ በተደረገ ምረመራ 1 ተማሪ በኮቪድ 19 መያዙን ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ ከሳምንት በኋላ በተደረገ ምርምራ ከ 50 በላይ ተማሪዎች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መመዝገባቸዉን ተናግረዋል፡፡
በቫይረሱ የሚያዙ ተማሪዎች ቁጥር የሚጨምር ከሆነ ትመህርት ቤቶች እንደሚዘጉ የተናገሩት ርዕሰ መምህሯ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸዉን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲጠቀሙ መደረግ አለበት ብለዋል፡፡
በዚህም በሁሉም ትመህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማጥለቅ የሚያስገድድ መመሪያ መውጣቱ ታውቋል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

