አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ጎጃም ዞን በማይጠብሪ ግንባር ህወሓትን እየተፋለመ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት፣ ለክልል ልዩ ሃይሎች፣ ሚሊሻ እና ፋኖ 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የዓይነት ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን የምዕራብ ጎጃም ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ይሁኔ ስጋት ለሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር አቶ ያለአለም ፈንታሁን አስረክበዋል።
ድጋፉ 342 በግ እና ፍየል፣ 14 ሰንጋዎች እና 708 ኩንታል የምግብ እህል መሆኑ ተገልጿል።
ዞኑ በቀጣይም ለመከላከያ ሰራዊት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ይሁኔ ተናግረዋል።
በመላኩ ገድፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

