Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መጪዎቹን የአደባባይ በዓላት የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በመተግበር ማክበር ይገባል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኅብረተሰቡ መጪዎቹን የመስቀል ደመራና በቀጣይ የሚከበሩ በዓላት ላይ የኮቪድ መከላከያ መንገዶችን በትኩረት ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስገነዘበ።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወቅታዊ የኮቪድ 19 ስርጭትን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

መድረኩ በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ የኮቪድ 19 ስርጭት መረጃ እና መከላከያ መንገዶችን አተገባበር ያለበት ሁኔታ ለማሳወቅ ያለመ ነው።

በተለይም በኮቪድ 19 ዙርያ የተሰበሰቡ መረጃዎች እና ቫይረሱን ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ለባለድርሻ አካላት በማቅረብ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ለማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version