Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኪነ-ጥበብና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የግድቡን ኃይል የማመንጨት ጅማሮ ዘካሪ ስራዎች እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ሃይል ማመንጨት አስመልክቶ የኪነ-ጥበብና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች አይረሴ ስራዎችእንዲሰሩ የግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ጥሪ አቀረበ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በሁለት ተርባይኖች የመጀመሪያውን ዙር ሃይል የማመንጨት ስራ ይጀምራል።
“ጥምረት ለፍትህ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ትስስር” ዓላማን የሚያስተዋውቅ የውይይት መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
የ”ጥምረት ለፍትህ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ትስስር” ዓላማ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚደረገውን ሁለገብ ተሳትፎ ማሳደግና ዲጂታል ንቅናቄ መፍጠር መሆኑም ተገልጿል።
የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ የግድቡን ግንባታ አጠናቆ ሃይል ማመንጨት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዕድገት መሰረት መጣል መሆኑን ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version