Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

‘ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት’ ሃገራዊ ዘመቻን ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)‘ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት’ ሃገራዊ ዘመቻን ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መቀላቀሉን የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶክተር መገርሳ ቃሲም አመለከቱ፡፡

በዘመቻው ቁጥሩ ከ10 ሺህ በላይ የሆኑ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና ተማሪዎች መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

“በአሁኑ ሰዓት በሃገራችን ላይ ያለአግባብ በአሜሪካ መንግስት በኩል እየተደረገ ያለውን ጫና በመቃወም እውነታውን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት መሆን ይገባዋል” ብለዋል ዶክተር መገርሳ፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም በማስከበር ግዳጅ ላይ መስዋትነት እየከፈለ ለሚገኘው የሃገር መከላከያ ሠራዊት 20 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ በመለገስ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡

በሃገር አቀፍ የተያዘው ዘመቻም እንዲሳካ ዩኒቨርሲቲው” ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ- መንግስት” ዘመቻን የተቀላቀለ ሲሆን÷ መላው የዩነቨርሲቲው መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና ተማሪዎች ከመስከረም 13 – 14/2014 ዓ.ም ድረስ መምህራንና ተማሪዎች በትምህርት ክፍላቸው፣ የአስተዳደር ሠራተኞች በምታገለግሉበት ዳይሬክቶሬት በመገኘት ድጋፋቸውን እንዲሰጡ እና ሃገራዊ ግዴታ እንዲወጡ ዶክተር መገርሳ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የ”ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ- መንግስት” ዘመቻ በመጪው ቅዳሜ መስከረም 15/2015 ዓ.ም ማጠቃለያ እንደሚከናወን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version