Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በህልውና ዘመቻው ለተሳተፉ በጎ ፈቃደኞች የምስጋና መረሃ ግብር ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህልውና ዘመቻውን ጥሪ ተቀብለው በጋይንት እና ጋሸና ግንባር ለሰራዊቱ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሲሰሩ ለቆዩ በጎፈቃደኛ ወጣቶች የደቡብ ጎንደር ዞን በደብረታቦር ከተማ የምስጋና እና የማበረታቻ መረሃ ግብር ተካሄደ፡፡
በጎ ፈቃደኞቹ በህልውና ዘመቻው ከሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እና የመንግስት ተቋማት የተውጣጡ ሲሆኑ÷ ከወራት በፊት ወደ ደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ወሎ መቄት ግንባር በመምጣት ለሰራዊቱ የሎጅስቲክና ሌሎች አቅርቦቶችን ግምባር ድረስ በመገኘት ደጀን ሆነው ሲያስተባብሩ የቆዩ ናቸው ተብሏል፡፡
የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና በግንባሩ የህዝብ ሎጅስቲክስ አስተባባሪ አቶ አወቀ ዘመነ እንደገለፁት÷ ሀገሪቱ ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ ላሳያችሁት ትብብር እና የህዝብ ደጀንነት ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል።
ወራሪው የትህነግ የሽብር ቡድን በአግባቡ እንዲቀጣ እና ራሱን እንዲመለከት በተሰራው ስራ ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ ከሰሩት ጀግንነት ጎን ለጎን የእናንተም ደጀንነት ከፍተኛ ነውና ምስጋና ይገባችኋል ያሉት ደግሞ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ ናቸው፡፡
እየተገኝ ያለው ድልም የብዙ ኃይሎች ድል ነው፤ እንዲህ አይነት ገድል ለማስመዝገብ ዘመናትን ይጠይቃል፤ የዚህ ዘመን ታሪክ ሰሪ በመሆናችሁም ልትኮሩ ይገባል ብለዋል፡፡
ከፊታችን ብዙ ስራዎች ይጠብቁናል እናንተም ድጋፍችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ሲሉም አሳስበዋል፡፡
በመረሃ ግብሩ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ በሰላም ሚኒስቴር አማካኝነት ከተለያዪ አካባቢዎች የተውጣጡ በጎ ፈቃደኞችን ጨምሮ ከደቡብ ጎንደር ዞንና ደብረታቦር ከተማ በህልውናው ዘመቻ የተሳተፉ ሁሉ ተመስግነዋል፡፡
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version