Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሚሊሻው ተሳትፎ የላቀ ቦታ የሚሰጠው ነው- ሌተናል ኮለኔል ለቺሳ መገርሣ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከውጭ አገር ጠላቶቻችን ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚውተረተረውን አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ በሚደረገው ትግል የሚሊሻው ተሳትፎ የላቀ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን የወሎ ግንባር ኢንዶክተሬሽን ዳይሬክተር ተወካይ ሌተናል ኮለኔል ለቺሳ መገርሣ ገለጹ፡፡
ሚሊሻው የሚሰጠውን የግዳጅ ቀጠና ጸሐይ፣ ዝናብ እና ውርጭ እየተፈራረቀበት ግዳጁን በአስተማማኝ ብቃት እየተወጣ ይገኛል ብለዋ ኮለኔሉ፡፡
አሸባሪውን የህወሓት ስብስብ ለመደምሰስ በሚደረገው ወኔ የተሞላበት ትግልም የሚሊሻ ተሳትፎ የላቀ ቦታ የሚሰጠው ነው ብለዋል።
ሚሊሻው ጠላት ሙሉ ለሙሉ ሳይደመሰስ ወደ ቤተሰቦቻችን አንመለስም በሚል ኢትዮጵያዊ እልህና ወኔ እየተፋለመ ይገኛል ያሉት ሌተናል ኮለኔል ለቺሳ÷ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከክልሎች ልዩ ኃይሎች ጋር በመናበብና በመቀናጀት የላቀ ጀብድ እየፈፀመ መሆኑን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል፡፡
ሚሊሻዎች የተሰለፉት በተወለዱበትና ባደጉበት ግንባር በመሆኑ መውጫ እና መግቢያ ቦታዎችን በሚገባ የሚለዩ ስለሆነ ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች በትግል ላይ ለሚገኙ የክልል ልዩ ኃይሎች አቅጣጫ በመጠቆም፣ በማሳየትና በመምራት በጠላት ላይ በበላይነት ድል ለመቀዳጀት ትልቅ ዕድል መፍጠሩንም ነው የተናገሩት፡፡
የጠላትን የእንቅስቃሴ አቅጣጫ በማወቅና በመጠቆምም ሚሊሻዎች ትልቅ ድርሻ እያበረከቱ መሆኑን የወሎ ግንባር ኢንዶክተሬሽን ዳይሬክተር ተወካይ ሌተናል ኮለኔል ለቺሳ መገርሣ ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 3 people, military uniform and outdoors
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share
Exit mobile version