አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 34ተኛው የአለም የቱሪዝም ቀን በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ በመከበር ላይ ይገኛል።
ዝግጅቱ ለሁለት ቀናቶች የሚቆይ ሲሆን፥ ከኤግዚቢሽን ዝግጅት በተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን የመጎብኘት እንዲሁም የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፥ በሀገር አቀፍ ደረጃ በቱሪዝሙ ዘርፍ እየተከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የሲዳማ ክልልም በርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ሀብቶች መገኛ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በጁንታው የተከፈተው ጦርነት በቱሪዝሙ ዘርፍ ላይ ጫና የፈጠረ ቢሆንም አንድነትን በማጠናከርና በማሸነፍ ይህን ፈተና ማለፍ ይቻላል ብለዋል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሒሩት ካሳው በበኩላቸው፥ ሀብቶችን በመለየትና በማልማት እንዲሁም ለቱሪዝሙ በማስተዋወቅ ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ ከሁሉም የሚጠበቅ ነው ብለዋል።
የቱሪዝሙ ዘርፍ የአለምን ህዝብ እንዲቀራረብ ከማድረግም ባሻገር ከፍተኛ የሆነ የገቢ አመንጪ መሆኑን ጠቅሰው፥ ሰላም ለዘርፉ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንና የኮሮና ቫይረስም ተፅዕኖ መፍጠሩን አንስተዋል።
የቱሪዝም አምባሳደር በመሆን ልዩ ተሸላሚ የሆኑት የሲዳማ ክልል ፕረዘዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ በዘርፋ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች የተለያዩ የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
“ቱሪዝም ለሁለንተናዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል በሚከበረው በዚህ በዓል ላይም የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
በብርሃኑ በጋሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ

+3
33,774
People Reached
960
Engagements
Boost Post
392
6 Comments
8 Shares
Like
Comment
Share
በብርሃኑ በጋሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

