አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለሐብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በማይጠብሪ ግንባር የሽብር ቡድኑን ህወሓት እየተፋለመ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት፣ የክልል ልዩ ሃይሎች፣ ሚሊሻ እና ፋኖ የድጋፍ እንዲሁም ለሰሜን ጎንደር ዞን ተፈናቃዮችየ25 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።
ባለሐብቱ ድጋፉን በደባርቅ ከተማ ተገኝተው ለሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ወ/ሮ ደብረወርቅ ይግዛው አስረክበዋል።
አቶ ወርቁ ÷ የሽብር ቡድኑን ህወሓት በአጭር ጊዜ ለማስወገድ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነት እና በቅንጅት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
በሽብር ቡድኑ ወረራ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች፣ መንግስታዊ ተቋማት እና ባለሃብቶች የበኩላቸውንእንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ወርቁ ÷ በቀጣይ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።
በተመሳሳይ የደንበጫ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር የሽብር ቡድኑን ህወሓት በማይጠብሪ ግንባር እየተፈለሙ ለሚገኙትመከላከያ ሰራዊት፣ የክልል ልዩ ሃይሎች ፣ሚሊሻ እና ፋኖ የ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል።
ወረዳው ሰንጋ፣ ፍየል እና በግ እንዲሁም የምግብ እህል ነው ድጋፍ ያደረገው።
ድጋፉን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አበባው አደራው ለምዕራብ ዕዝ መረጃና ደህንት ሃላፊ ኮሎኔል እስራኤል ተፈራ አስረክበዋል።
በቀጣይም የህልውና ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድረስ የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንደሚያደርጉ አቶ ወርቁ ቃል ገብተዋል።
በመላኩ ገድፍ

