አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለስ የእንግሊዝ ፓርላማ አባልና በፓርላማው የኢትዮጵያ ጉዳይ ሊቀመንበር ከሆኑት ላውረንስ ሮበርትሰን ጋር የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
በውይይታቸውም አምባሳደር ተፈሪ የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታዎችን የተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነትን ለማመቻቸት እንዲቻል የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ አስተላልፎ የነበረ መሆኑን አንስተዋል።
አያይዘውም ወቅታዊ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ የስደተኞችን ሁኔታ የተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አምባሳደር ተፈሪ ሽብረተኛው የህወሓት ቡድን በአፋርና አማራ ክልሎች ባደረገው ወረራ ሚሊየኖች መፈናቀላቸውን ጠቅሰው፥ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
በተያያዘም ሽብረተኛው የህወሓት ቡድን በአፋርና አማራ ክልሎች የፈጸመው ወረራ ለኢትዮጵያም ሆነ ለቀጠናው አለመረጋጋትን የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፥የእንግሊዝ የፓርላማ አባላትም ሆነ መላው የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማውገዝ አንደሚገባው አጽንኦት ሰጥተው መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share

