አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በመስቀል የደመራ በዓል ዕለት ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ እና ለክትባት ፈለጊዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ያለውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የበሽታውን የመከላከያ መንገዶችን በአንክሮ ከመከተልና መተግበር እኩል ክትባቱን ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸው ሁሉ እንዲከተቡ ማድረግና የምርመራ አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ ተግባራት ናቸው ተብሏል፡፡
በመሆኑም እንደ ደመራ ፤ ኢሬቻ እና ሌሎችም ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች እነዚህ አገልግሎቶች የሚሰጡ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
የደመራ በዓልን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ በሚመጡበት ጊዜ በሁሉም መዳረሻዎች ላይ ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ የሚሰጥ መሆኑ ተነስቷል፡፡
እንዲሁም በስቴዲየም መግቢያ ክትባቱ የሚሰጥ በመሆኑ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል አገልግሎቱን ማግኘት ይችላል ተብሏል፡፡
ስለ ሕብረተሰብ ጤና አደጋ የኮቪድ-19 ጨምሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እንዲሁም ጥቆማ ለመስጠት 952 ወይም 8335 ላይ ደውለው የጤና ባለሙያዎችን ማነጋገር እንደሚቻል ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!