Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ከዋግ ኸምራ ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በህወሓት የሽብር ቡድን ተፈናቅለው በዞኑ እብእናት ከተማ ለሚገኙ 16 ሺህ ለሚሆኑ የዋግ ኸምራ ተፈናቃዮች 700 ኩንታል የምግብ እህል በደቡብ ጎንደር ዞን ከሚገኙ ወርዳዎች በማሰባሰብ ድጋፍ ተደርጓል።
የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ ፥በሽብር ቡድኑ ውድመት በችግር ላይ ብንሆንም ለመጀመሪያ ዙር የሚሆን ለዋግ ኸምራ ወገኖቻችን ከጎናችሁ ነን ለማለት ይህን ድጋፍ አድርገናል ነው ያሉት።
በተጨማሪም በተከዜ ግንባር ለሚገኙ ለአማራ ልዩ ሀይል፣ ፍኖ እና ሚሊሻዎች የሚሆን የእርድ ሰንጋዎችን በግ እና ፍየሎች ድጋፋ ተደርጓል ብለዋል።
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version