Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፋር ክልል መስከረም 20/2014 አዲስ መንግስት ይመሰረታል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል መንግስት መስከረም 20/2014 ዓ.ም አዲሱን መንግስት እንደሚመሰርት የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አሚና ሴኮ ገለፁ፡፡
በ6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ለክልል ምክር ቤት ተወዳድረው ድምፅ ያገኙ አባላት የ6ኛ የስራ ዘመን የመጀመሪያ ጉባኤያቸውን መሰከረም 20 ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
በዚሁ ወቅት ነባሩን የምክር ቤት አባላት በመሸኝት÷ አዲስ በተመረጡት የምክር ቤት አባላት በመተካት አዲስ መንግሰት ይቋቋማል ሲሉ አፈ ጉባኤ ተናግረዋል ሲል የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version