አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በአሸባሪው ህወሓት ምክንያት በተወሰኑ የአገሪቱ አካባቢዎች የእርሻ ስራዎች ቢስተጓጎሉም እንደ ሀገር የምርት እጥረት አይገጥመንም ሲሉ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ ገለጹ፡፡
ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፥ መንግስት ሳይፈልግ በገባበት ጦርነት ሳቢያ በተወሰኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች የእርሻ ስራዎች ቢስተጓጎሉም እንደ ሀገር የምርት እጥረት አይገጥመንም ብለዋል፡፡
በተለይ ምርታማ በሆኑ የአገሪቱ አካባቢዎችም የተሻለ ምርት ለማግኘት የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በአገር ደረጃ በ2013/14 ምርት እቅድ ዘመን 13 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን 400 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተው ፥ይህን ዕቅድ ለማሳካትና በአሸባሪው ህወሓት ምክንያት እርሻ ስራ በተስጓጎለባቸው የተወሰኑ አካባቢዎች የሚገኘውን ምርት ለማካካስ ጭምር ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share