Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአማራ ክልል የ2014 በጀት ከ80 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣7ኛ ዓመት 18ኛ መጨረሻ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ የክልሉን የ2014 በጀት 80 ቢሊየን 104 ሚሊየን 669 ሺህ 397 ብር አጽድቋል።

የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ጥላሁን መሃሪ÷ በጀቱ መንግሥት ለዜጎች ፍትሐዊና ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የ2014 በጀት አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን ወረራ የፈጸመባቸውን አካባቢዎች ለማቋቋም፣ የ10 ዓመታት የመሪ እቅድ የልማት ግቦችን ለማሳካት፣ አዳዲስ መሥሪያ ቤቶችን፣ የእኩል ሥራን እኩል ክፍያን፣ የካፒታል ወጪን፣ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሚያስችል ነው ብለዋል።

በጀቱ የተጀመሩ እና በቀጣይ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ኀላፊው ማስታወቃቸውን አሚኮ ዘግቧል።

የተመደበው በጀትም ከፌዴራል እና ከክልሉ ገቢ የሚገኝ ሲሆን÷ ሁሉም መሥሪያ ቤቶችና የሚመለከታቸው አካላት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ መጠቀም እንዳለባቸው ዶክተር ጥላሁን አሳስበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version