አዲስ አበባ፣ መስረም 19፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ሦስተኛ የስራ ዘመን የመጀመሪያ ዓመት ጉባኤ ማካሄድ ጀምሯል።
ጉባኤው የምክር ቤቱን አፈጉባኤና የአስተዳደሩን ከንቲባ ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በቻርተር መተዳደር ከጀመረችበት ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስተኛ ዙር በተካሄደው ምርጫ ያሸነፉ 189 ተወዳዳሪዎች የምክር ቤቱን ወንበር ይረከባሉ።
በቀጣይ አምስት ዓመት ህዝብን በቅንነትና በታማኝነት ያገለግላሉ ተብሎ የታመነባቸው የምክር ቤቱ ተመራጮች፥ ለሥራቸው የሚያግዛቸውን ስልጠና ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲወስዱ መቆየታቸው ይታወሳል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!