Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቱኒዚያዉ ፕሬዚደንት በአገሪቱ የመጀመሪያዋን ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሾሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ስልጣን ከያዙ ገና ሁለት ወር ገደማ የሆናቸው የቱኒዚያዉ ፕሬዚደንት ካይስ ሳኢድ፥ ናጅላ ን ሮምዳንን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር አድረገዉ ሾሙ።

የቱኒዚያው ፕሬዚደንት በትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያ ሆነው ሲሰሩ የዓለም ባንክ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ ያስፈጸሙትንና የጆኦፊዚክስ ፕሮፌሰር የሆኑትን ናጅላ ቡደን ሮምዳንን የአገሪቱ የመጀመሪያ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው በመሾም አዲስ መንግስት እንዲመሰርቱ ጠይቀዋቸዋል።

ፕሬዚደንቱ በሀገሪቱ ለመጀመሪ ጊዜ ሴት ጠቅላይ ሚኒስቴር መሾማቸው ታሪካዊ ውሳኔ እንደሆነና በዚህም ክብር እንደሚሰማቸዉ ተናግረዋል።

ፕሬዚደንት ሳይድ እንዳሉት፥ የአዲሱ መንግስት ዋና ተልዕኮ “በብዙ የመንግስት ተቋማት ውስጥ የተስፋፋውን ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የጤና ፣ የትራንስፖርትና የትምህርት አገልግሎትን ጨምሮ በሁሉም መስኮች ለቱኒዚያውያን መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።

ቱኒዚያ በተከተለችው የዴሞክራሲያዊ ሽግግር ሂደት ዓለም አቀፋዊ ሽልማቶችን ያሸነፈች አገር ብትሆንም፥ የዜጎቿ ዉስብስብ የፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር መሻሻል አላሳየም ተብሏል።

ምንጭ ፡- አልጄዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version