Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደቡብ ወሎ ዞን 12 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዞኑ የታቀደውን 12 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማሳካት አረምን የመከላከል ስራው ሳይስተጓጎል መቀጠሉን የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው ሀላፊ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ እስከ 30 በመቶ ምርት ሊጎዳ የሚችለውን አረም በመከላከል በኩል በርካታ ሰራዎች ተሠርተዋል፡፡
በዚህም በ1ኛ ዙር የአረም ስራ ከ423 ሺህ በላይ መሬት መታረሙን የገለጹት ሀላፊው አፈጻጸሙም 97 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል።
የሁለተኛ ዙር አረም ስራው 61 በመቶ የደረሰ ሲሆን÷ በተግባሩ ሊታይ የሚችለውን የምርት መቀነስ ስጋት ያስቀረ ነው ብለዋል።
እርሻን ደጋግሞ በማረም የተሻለ ምርት እንዲገኝ በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
ዞኑ በ2013/14 የምርት ዘመን ከ12 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ያቀደ ሲሆን÷ ለዚህም ከ433 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሰብል ተሸፍኗል።
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version