Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሽብርተኛውን የትህነግ ቡድን እየተፋለሙ ያሉ የጀግኖችን ገድል ለመድገም ተዘጋጅተናል – የኮማንዶ ሠልጣኞች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብላቴ ልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የ37ኛ ዙር መሰረታዊ ኮማንዶ ሠልጣኞችን አቀባበልና የስልጠና መክፈቻ መርኃግብር አካሂዷል፡፡
የማሰልጠኛ ማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ዋለልኝ ታደሰ “በትልቅ ሞራልና ወኔ ሀገር ስትደፈር አናይም ብላችሁ በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ክቡር የሆነውን የውትድርና ሙያ አጠናቃችሁ የመሰረታዊ ኮማንዶ ስልጠናን ለመሰልጠን ከተለያዩ ማሰልጠኛዎች ወደ ማሰልጠኛ ማዕከላችን የተቀላቀላችሁ ሀገራችሁ ትኮራባችኋለች” ብለዋል፡፡
በማሰልጠኛ ማዕከሉ የሚሰጡትን የመሰረታዊ ኮማንዶ ስልጠናዎች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ሰልጠናችሁን በተገቢው ሁኔታ በማጠናቀቅ የሀገር ኩራትና የክፉ ቀን ባለውለታዋ መሆን ይኖርባችኋል ነው ያሉት፡፡
ሰልጣኞች ለሰንደቅ ዓላማና ለሕዝብ መሰዋት ክብር ነው፤ ስልጠናችንን በቁርጠኝነትና በወኔ ለመሰልጠን ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
ሽብርተኛውን የትህነግ ቡድን በግንባር እየተፋለሙ ያሉ የጀግኖችን ገድል ለመድገም ዝግጁ እንደሆኑ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version