አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው በከፈተው ጦርነት ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞን ተፈናቅለው በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች የተጠለሉ ተፈናቃዮችን ወደ መጠለያ ለማስገባት እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡
አጠቃላይ 350 ሺህ የሚደርሡ ተፈናቃዮች በከተሞች ተጠልለዉ መቆየታቸዉን የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የአደጋ ምላሽና ክትትል ቡድን መሪ አቶ ታዬ ጌታቸው ተናግረዋል፡፡
ከእነዚህ ዜጎች መካከል ወደ 14 ሺህ የሚጠጉት ብቻ ናቸው የቀጥታ ድጋፍ እያገኙ የሚገኙት ብለዋል ቡድን መሪዉ፡፡
ቀሪዎቹ በማህበረሰቡ ውስጥ ተጠግተው አልያም ቤት ተከራይተው እንደሚኖሩ ተጠቅሷል።
የተፈናቃዬቹ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ያሉት አቶ ታዬ÷ 96ሺህ ዜጎች ምንም ድጋፍ ያላገኙ መሆናቸውን አንስተዋል ፡፡
ከእነዚህ ውጭ ያሉት ግን በፌዴራል ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እንዲሁም በአመልድ እና ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ እያገኙ ናቸው ብለዋል፡፡
መጪው የትምህርት ጊዜ ስለሆነ ትምህርት ቤቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ተፈናቃዮቹን ወደ ጊዜያዊ መጠለያ ለማዘዋወር እንቅስቀሴ ተጀምሯል ነው ያሉት፡፡
መጠለያዎቹን ለመስራት የሚፈጀው ጊዜ ከግምት ዉስጥ ገብቶ በጊዜያዊነት በቤቶች ውስጥ በኪራይ እንዲቀመጡ እየተሰራ ነው ብለዋል አቶ ታዬ፡፡
መጠለያዎቹን ከወዲሁ ለማዘጋጀት ቦታ መለየቱን አንስተዋል፡፡
በሀብታሙ ተ/ስላሴና እሸቱ ወ/ሚካኤል
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

