አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንስቲትዩቱ ዋና መ/ቤት ሁሉም የኢንስቲትዩቱ አመራሮችናሠራተኞች በተገኙበት የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጭ ቤተ መንግስት ዘመቻ ተቀላቅላዋል፡፡
መድረኩን የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ተረፈ ዘለቀ ፥ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን እውነታ ማስረዳትና የህወሐት ቡድን እየፈጸማቸው ያሉ እኩይ ተግባራት ማጋለጥ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን ኃላፊነት ነው ብለዋል።
በመሆኑ እኛም የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ይህንን በጎ ዓላማ በመደገፍ ሀገራዊ ግዴታችንን ለመወጣት ዘመቻው ተቀላቅለናል ነው ያሉት፡፡
የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ዘመቻ ዓላማን በተመለከተም የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ኮንሰልታንት አቶ እሸቱ ብሩ ገለፃ አድርገዋል።
ሁሉም የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሠራተኞች በተዘጋጀው ደብዳቤ ላይ ፊርማቸውን በማኖር የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ዘመቻ መቀላቀላቸውን ከኢንስቲዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!