አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ ሄለን ደበበ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በክልልነት የመደራጀት ህዝበ ውሳኔ ጊንቦ ምርጫ ክልል ኡፋ ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል።
ህዝበ ውሳኔው ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሽግግር ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታልም ብለዋል ዋና አፈ ጉባኤዋ።
በኢትዮጵያ እውነተኛ ፌደራሊዝምን ለማስፈን እየተካሄደ የሚገኘው ህዝበ ውሳኔ አዎንታዊ ሚና እንደሚያበረክት መናገራቸውን ኢዜአ እና ደሬቴድ ዘግበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

