አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ጥሩዬ አሠፌ ወሎ ግንባር ከሚገኙ ሴት የሠራዊት አባላት ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በግንባሩ ያሉ ሴቶች በተልዕኮ አፈፃፀም ውስጥ ላሳዩአቸው ጥንካሬዎች እውቅናና ክብር መስጠትን አላማው ያደረገ ነው ።
በመድረኩ የሴቶች እኩልነትና የእንችላለን ስሜት ከቃል ባለፈ በተግባር የህይወት መስዋዕትነትን በሚጠይቀው ውትድርና ውስጥ ጭምር በብቃት እየታየ ስለመሆኑ በተሳታፊ ሴት የሰራዊት አባላቱ ተገልጿል።
አሸባሪውን የህወሓት ሀይል በመደምሰሡ ረገድ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሴቶች ከጠላት ጋር የጨበጣ ውጊያ በመግጠምና ቦንብ ሲጨርሡ በድንጋይ ምሽግ በማስለቀቅ ጭምር ጀግንነታቸውን ማሳየታቸው ተነግሯል።
በግንባር የሚገኙ ሴት የሠራዊት አባላት የአውደ ውጊያ ጥንካሬ በአሁኑ ወቅት ለወንድ የሠራዊት አባላቱም ጭምር የተሻለ መነሳሳትን እየፈጠረ እንዳለም በውይይቱ ተነስቷል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሯ ሜጀር ጀነራል ጥሩዬ አሠፌ ፣ ጀግንነት ለኢትዮጵያውያን ሴቶች ቀድሞውንም መገለጫቸው ነው ሲሉ ገልጸዋል።
እናንተም የሀገራችሁን ፍቅር በመስዋዕትነት ጭምር እየገለፃችሁና ይህንኑ ጀግንነት እያስቀጠላችሁ በመሆኑ ስራችሁ ምንጊዜም በታሪክ ሲነገር የሚኖር ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share