አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በሐረሪ ክልል የተካሄደው ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ስጋት በሰላም መጠናቀቁን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ነስሪ ዘካሪያ እንደተናገሩት÷ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ስጋት ተጠናቋል።
ምርጫው በሰላም እንዲከናወን የክልሉ ፖሊስ ከፌደራል ፖሊስና ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።
የምርጫው ውጤት እስከሚለይ ባለው ሂደትም የተጀመረው የጥበቃ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።
ለምርጫው በሠላም መጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ የህግ አካላትና ህዝቡን አመስግነው÷ በቀጣይም ትብብራቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

