Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ዶክተር ፍትህ ወልደሰንበት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የአፍሪካ እጅ ኳስ ኮንፌዴሬሽን የዞን አምስት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።
ዶክተር ፍትህ ÷በበይነ መረብ በተደረገ የምስራቅ አፍሪካ ዞን አምስት የምርጫ ኮንግረስ ስብሰባ ላይ ነው የኡጋንዳውን እጩ ስድስት ለሶስት በሆነ የድምፅ ብልጫ የዞን አምስት ፕሬዝደንት አድርጎ መርጧቸዋል።
ዶክተር ፍትህ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽንን ላለፋት አምስት ዓመታት መምራታቸውን ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version