Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኮንፈረንስ ስኬታማነት በትኩረት እየሰራን ነው- የብሄራዊ ኮሚቴው

አዲስ አበባ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፋ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኮንፈረንስ ስኬታማነት በትኩረት እየሰራን ነው ሲሉ የብሄራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ ተናገሩ፡፡
የአለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ልማት ጉባኤ አዘጋጅ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ኮሜቴ ዝግጅቱን የተመለከተ ስብባውን ያካሄደ ሲሆን ÷የብሄራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር አህመዲን የቴሌኮም ኮንፈረንሱ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካንም የሚወክል ነው ብለዋል፡፡
በአፍሪካ ለመጀሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተነስቷል።
ዶክተር አህመዲን መሐመድ ÷ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኮንፈረንስ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከዓለም ሀገራት ልምድ የምንለዋወጥበትና የኢትዮጵያን ገፅታ የምንገነባበት ይሆናል ብለዋል፡፡
ለዝግጅቱ በስኬት መጠናቀቅ የሚመለከታቸው ሁሉ በትብብር እንዲሰሩ አሳስበዋል።
የብሄራዊ ኮሚቴው ፀሃፊ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ ÷ ጉባኤው የቴሌኮሙኒኬሽን ልማት የወደፊት አቅጣጫዎች የሚነደፍበት በመሆኑ ኢትዮጵያ ለዘርፉ ማሻሻያዎች የሚሆኑ ልምዶችን ትቀስማለች ብለዋል።
የዓለም አቀፉ የቴሌኮም ልማት ጉባኤ በየ4 ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን÷ 8ኛው ጉባኤ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከግንቦት 27 ቀን 2014 ጀምሮ እንደሚካሄድ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version