አዲስ አበባ፣መስከረም 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በሐረሪ ክልል በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደት በመጠናቀቁ የድምጽ መስጫ ሳጥኖች ወደ ምርጫ ክልል በመጓጓዝ ላይ መሆናቸውን የክልሉ ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ጊዜያዊ ውጤቶችም በየምርጫ ጣቢያዎች መለጠፋቸውም ተገልጿል።
የክልሉ ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ቦጋለ እንዳሉት÷ የድምጽ መስጠት ሒደቱ በሰላም ካለቀ በኋላ በየጣቢያዎቹ የተካሄደው የድምፅ ቆጠራ ተጠናቋል።
በዛሬው ዕለትም የድምጽ መስጫ ሳጥኖች ወደ ምርጫ ክልል የማጓጓዝ ስራ እየተካሔደ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
መራጩ ሕዝብም በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻው ውጤት እስኪገለጽ እንዲጠባበቅ ጠይቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!