አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት የተመሰረተው አዲሱ የክልሉ መንግሥት መዋቅር የአማራን ሕዝብ ወሳኝ ጥያቄ ለመመለስ እንዲሰራ ያስችለዋል ሲሉ የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ አስታወቁ።
አዲስ የተመሠረተውን የክልሉን መንግሥት አስመልክቶ ዛሬ ማብራሪያ የሰጡት የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በአዲስ መልኩ የተዋቀረው የክልሉ ካቢኔ የክልሉን ሕዝብ ችግር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት።
75 በመቶ በአዲስ የተተኩት የአማራ ክልል የሥራ ኀላፊዎች በትምህርት ዝግጅታቸው፣ በሥራ ልምዳቸው፣ በዕድሜያቸውም ኾነ በሥነ ምግባራቸው ብቁ በመሆናቸው ክልሉ የገጠመውን ዘርፈ ብዙ ችግር ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው የተናገሩት።
አዲሶቹ ተሿሚዎች የአማራ ሕዝብ የተጋረጠበትን አደጋ የመቀልበስና የአማራ ሕዝብን ጥያቄ ለመፍታት የሚያስችል እውቀት እና ችሎታ ያላቸው መሆናቸውን አቶ ግዛቸው መግለጻቸውን የአሚኮ ዘገባ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!