አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ከሮተሪ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በትምህርቱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
የመግባቢያ ሰነዱ በንጹህ ውሃ አቅርቦትና በሌሎችም ትምህርት ነክ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት በትምህርት ቤቶች የሚስተዋለውን የውሃና ንጽህና አጠባበቅ ችግሮች ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ስምምነቱም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተቀናጀ መንገድ ስራዎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመተግበር እንደሚያስችልም ገልፀዋል፡፡
የሮተሪ ኢትዮጵያ ሊቀመንበር ተሾመ ከበደ በበኩላቸው÷ በትምህርት ቤቶች የውሃ አቅርቦቶች እንዲኖር የሚያሰችል ፕሮጀክት መዘጋጀቱን ገልፀው በአጭር ጊዜ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅቶች እያደረጉ እንዳለም መግለፃቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሮተሪ ኢንተርናሽናል የተለያዩ ስራዎችን በትምህርት ዘርፉ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!