አዲስ አበባ፣መስከረም 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በአልን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ወይዘሮ አዳነች በማህበራዊ የትስስር ገፃቸዉ ላይ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ፥ ”የእርቅ፣ የይቅርታ፣ የሰላም እና የወንድማማችነት እሴቶች መገለጫ ለሆነው የኢሬቻ በአል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
ነገ በሆራ ፊንፊኔ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ ለመታደም ወደ ከተማችን፣ ከተማችሁ እንኳን በደህና መጣችሁ።
ኢሬቻ መሻገር ነው፡፡ ኢሬቻ ከፈተናዎች በላይ መረማመድ ነው፡፡
ኢሬቻ የድል ብስራት ነው፡፡ ክረምትን በበጋ መተካት ብቻ ሳይሆን ፈተናን በአስደናቂ ድል፣ ችግሮችን በሁሉን አቀፍ መፍትሄ፣ አይቻልምን በመቻል የመሻገር፣ የለውጥ ከፍታ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የሆራ ፊንፊኔን በዓል በድምቀት እንድናከብር በዓሉ የሚከበርበትን ቦታ በማጽዳት፣ እንግዶችን ተቀብሎ በማስተናገድ፣ ከተማውን በማስዋብ፣ ሰላምና ጸጥታን በማስከበር ላይ ለተሳተፉ የከተማችን ነዋሪዎች እና ተቋማትን ሁሉ በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁም ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!