Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፊሊፒንሱ ፕሬዝደንት ራሳቸውን ከፖለቲካ እንደሚያገሉ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የፊሊፒንሱ  ፕሬዚደንት  ራሳቸውን  ከፖለቲካ እንደሚያገሉ አስታወቁ

የፊሊፒንሱ ፕሬዚደንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ለምክትል ፕሬዚደንትነት ጭምር እንደማይወዳደሩና ራሳቸውን ከፖለቲካ እንደሚያገልሉ ተናግረዋል።

በአገሪቱ ህገ መንግሥት መሰረት ለሁለተኛ ጊዜ  ለፕሬዚደንት ምርጫ መወዳደር የማይችሉት የፊሊፒንሱ ፕሬዚደንት ሮዴርጎ ዱቴርቴ ፥ ባለፈው ዓመት ምክትል ፕሬዚደንትነት እወዳደራለሁ ብለው ነበር።

ፕሬዚደንቱ ራሳቸውን  ከፖለቲካ ለማግለል የወሰኑት በእሳቸው ምትክ  ሴት ልጃቸ ወደ ፖለቲካዉ ዓለም በማምጣት ለፕሬዚደንትነት ሊወዳደሩ ይችላሉ የሚል ወሬ እየተናፈሰ ባለበት ወቅት መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

አሁን ላይ የፊሊፒንሳዉያንን ስሜት የሚመጥን የአመራር ብቃት ላይ አይደለሁም ነው ያሉት ፕሬዚደንቱ።

አወዛጋቢዉ ፕሬዚደንት ሮዴርጎ ዱቴርቴ በአዉሮፓዉያኑ 2016 ወደ ሥልጣን የመጡ ሲሆን፥  በሀገሪቱ ባካሄዱት “የአደገኛ ዕፅ  ጦርነት” ጋር ተያይዞ 12 ሺህ ዜጎች እንዲገደሉ አድርገዋል በሚል ስማቸው ይነሳል።

በፊሊፒንስ ሕገ መንግሥት  መሰረት ተመራጩ ፕሬዚደንት የስድስት ዓመት የሥልጣን ዘመን ብቻ እንዲኖራቸዉ ይፈቅዳል።

በሚኪያስ አየለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
May be an image of 1 person and standing
0
People Reached
12
Engagements
Boost Post
12
Exit mobile version